ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 13:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ምኞት ስትፈጸም ነፍስን ደስ ታሰኛለች፤ተላሎች ግን ከክፋት መራቅን ይጸየፋሉ።

20. ከጠቢብ ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤የተላሎች ባልንጀራ ግን ጒዳት ያገኘዋል።

21. መጥፎ ዕድል ኀጢአተኛን ይከታተላል፤ብልጽግና ግን የጻድቃን ዋጋ ነው።

22. ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ትቶ ያልፋል፤የኀጢአተኞች ሀብት ግን ለጻድቃን ይከማቻል።

23. የድኾች ዕርሻ የተትረፈረፈ ምርት ያስገኛል፤የፍትሕ መጓደል ግን ጠራርጎ ይወስደዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 13