ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 11:17-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፤ጨካኝ ግን በራሱ ላይ መከራ ያመጣል።

18. ክፉ ሰው የሚያገኘው ትርፍ መቅኖ የለውም፤ጽድቅን የሚዘራ ግን አስተማማኝ ዋጋ ያገኛል።

19. እውነተኛ ጻድቅ ሕይወትን ያገኛል፤ክፋትን የሚከተል ግን ወደ ሞቱ ይጓዛል።

20. እግዚአብሔር ልበ ጠማሞችን ይጸየፋል፤በመንገዳቸው ነቀፋ በሌለባቸው ሰዎች ግን ደስ ይሰኛል።

21. ክፉ ሳይቀጣ እንደማይቀር ዕወቅ፣ጻድቃን ግን በነጻ ይሄዳሉ።

22. በእርያ አፍንጫ ላይ እንደ ተሰካ የወርቅ ቀለበት፣ማስተዋል የጐደላት ቆንጆ ሴት እንዲሁ ናት።

23. የጻድቃን ምኞት ምንጊዜም ፍጻሜው ያማረ ነው፤የክፉዎች ተስፋ ግን በቊጣ ያከትማል።

24. አንዱ በለጋስነት ይሰጣል፤ ሆኖም ይበልጥ ያገኛል፤ሌላው ያለ መጠን ይሰስታል፤ ግን ይደኸያል።

25. ለጋስ ይበለጽጋል፤ሌሎችን የሚያረካም ራሱ ይረካል።

26. በድብቅ እህል የሚያከማቸውን ሕዝብ ይረግመዋል፤አውጥቶ የሚሸጥ ግን በረከት ይጐናጸፋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 11