ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 10:15-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤ድኽነት ግን የድኾች መጥፊያ ናት።

16. የጻድቃን ደመወዝ ሕይወት ታስገኝላቸዋለች፤የክፉዎች ትርፍ ግን ቅጣትን ታመጣባቸዋለች።

17. ተግሣጽን ነቅቶ የሚጠብቅ የሕይወትን መንገድ ያሳያል፤ዕርምትን የማይቀበል ግን ሌሎችን ወደ ስሕተት ይመራል።

18. ጥላቻውን የሚሸሽግ ሐሰተኛ አንደበት ያለው ነው፤ሐሜትን የሚዘራ ሁሉ ተላላ ነው።

19. ከቃላት ብዛት ኀጢአት አይታጣም፤አንደበቱን የሚገታ ግን ጠቢብ ነው።

20. የጻድቅ አንደበት የነጠረ ብር ነው፤የክፉ ሰው ልብ ግን ርባና የለውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 10