ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 10:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የሰሎሞን ምሳሌዎች፤ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ተላላ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል።

2. ያላግባብ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።

3. እግዚአብሔር ጻድቁ እንዲራብ አያደርግም፤የክፉዎችን ምኞት ግን ያጨናግፋል።

4. ሰነፍ እጆች ሰውን ያደኸያሉ፤ትጉ እጆች ግን ብልጽግናን ያመጣሉ።

5. ሰብሉን በበጋ የሚሰበስብ ጠቢብ ልጅ ነው፤በመከር ጊዜ የሚተኛ ግን ውርደት ይከተለዋል።

6. በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ነው፤መዓት ግን የክፉዎችን አፍ ይዘጋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 10