ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 4:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽ!እንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ዐይኖችሽእንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው፤ጠጒርሽም ከገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ፣የፍየል መንጋ ነው።

2. ጥርሶችሽ ወዲያው ተሸልተው፣ከመታጠቢያ እንደ ወጡ የበግ መንጋ ናቸው፤ሁሉም መንታ መንታ የወለዱ፣ከመካከላቸውም መካን የሌለባቸው ናቸው።

3. ከንፈሮችሽ ቀይ የሐር ፈትል ይመስላሉ፤አፍሽም ውብ ነው፤ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጒንጮችሽ፣ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 4