ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 3:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣በሚዳቋና በሜዳ ዋልያ አማጥናችኋለሁ።

6. ከከርቤና ከዕጣን፣ከነጋዴም ቅመማ ቅመም ሁሉ በተዘጋጀ ሽቱ፣መዐዛዋ የሚያውድ፣እንደ ጢስ ዐምድ ከምድረ በዳ የምትዋጣው ይህች ማን ናት?

7. እነሆ፤ የሰሎሞን ሠረገላበታዋቂዎቹ የእስራኤል መኳንንት፣ሥልሳ ጦረኞች ታጅባለች፤

8. ሁሉም ሰይፍ የታጠቁ፣ሁሉም በጦርነት የተፈተኑ ናቸው፤የሌሊት አደጋን ለመከላከልም፣እያንዳንዳቸው ሰይፋቸውን በወገባቸው ታጥቀዋል።

9. ንጉሥ ሰሎሞን የራሱን ሠረገላ ሠራ፤የሠራውም ከሊባኖስ በመጣ ዕንጨት ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 3