ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሌሊቱን ሙሉ በአልጋዬ ላይ ሆኜ፣ውዴን ተመኘሁ፤ተመኘሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።

2. ተነሥቼ ወደ ከተማዪቱ እወጣለሁ፤በዋና ዋና መንገዶችና በአደባባዮች እዘዋወራለሁ፤ውዴንም እፈልገዋለሁ፤ስለዚህም ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።

3. በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣የከተማዪቱ ጠባቂዎች አገኙኝ፤እኔም፣ “ውዴን አይታችኋል?”አልኋቸው።

4. ከእነርሱ ጥቂት ዕልፍ እንዳልሁ፣ውዴን አገኘሁት፤ ያዝሁት፤ወደ እናቴ ቤት እስካመጣው፣በማሕፀን ወደ ተሸከመችኝም ዕልፍኝእስካገባው ድረስ አልለቀውም።

5. እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣በሚዳቋና በሜዳ ዋልያ አማጥናችኋለሁ።

6. ከከርቤና ከዕጣን፣ከነጋዴም ቅመማ ቅመም ሁሉ በተዘጋጀ ሽቱ፣መዐዛዋ የሚያውድ፣እንደ ጢስ ዐምድ ከምድረ በዳ የምትዋጣው ይህች ማን ናት?

7. እነሆ፤ የሰሎሞን ሠረገላበታዋቂዎቹ የእስራኤል መኳንንት፣ሥልሳ ጦረኞች ታጅባለች፤

8. ሁሉም ሰይፍ የታጠቁ፣ሁሉም በጦርነት የተፈተኑ ናቸው፤የሌሊት አደጋን ለመከላከልም፣እያንዳንዳቸው ሰይፋቸውን በወገባቸው ታጥቀዋል።

9. ንጉሥ ሰሎሞን የራሱን ሠረገላ ሠራ፤የሠራውም ከሊባኖስ በመጣ ዕንጨት ነው።

10. ምሰሶዎቹን ከብር፣መደገፊያውንም ከወርቅ ሠራ፤መቀመጫውም በሐምራዊ ሐር የተሸፈነ ነው፤ውስጡም በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፣አምሮ የተለበጠ ነው።

11. እናንት የጽዮን ቈነጃጅት ውጡ፤ንጉሥ ሰሎሞን አክሊሉን ደፍቶ እዩት፤ዘውዱም ልቡ ሐሤት ባደረገባት፣በዚያች በሰርጉ ዕለት፣እናቱ የደፋችለት ነው።