ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 3:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ከእነርሱ ጥቂት ዕልፍ እንዳልሁ፣ውዴን አገኘሁት፤ ያዝሁት፤ወደ እናቴ ቤት እስካመጣው፣በማሕፀን ወደ ተሸከመችኝም ዕልፍኝእስካገባው ድረስ አልለቀውም።

5. እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣በሚዳቋና በሜዳ ዋልያ አማጥናችኋለሁ።

6. ከከርቤና ከዕጣን፣ከነጋዴም ቅመማ ቅመም ሁሉ በተዘጋጀ ሽቱ፣መዐዛዋ የሚያውድ፣እንደ ጢስ ዐምድ ከምድረ በዳ የምትዋጣው ይህች ማን ናት?

7. እነሆ፤ የሰሎሞን ሠረገላበታዋቂዎቹ የእስራኤል መኳንንት፣ሥልሳ ጦረኞች ታጅባለች፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 3