ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 3:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሌሊቱን ሙሉ በአልጋዬ ላይ ሆኜ፣ውዴን ተመኘሁ፤ተመኘሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።

2. ተነሥቼ ወደ ከተማዪቱ እወጣለሁ፤በዋና ዋና መንገዶችና በአደባባዮች እዘዋወራለሁ፤ውዴንም እፈልገዋለሁ፤ስለዚህም ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።

3. በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣የከተማዪቱ ጠባቂዎች አገኙኝ፤እኔም፣ “ውዴን አይታችኋል?”አልኋቸው።

4. ከእነርሱ ጥቂት ዕልፍ እንዳልሁ፣ውዴን አገኘሁት፤ ያዝሁት፤ወደ እናቴ ቤት እስካመጣው፣በማሕፀን ወደ ተሸከመችኝም ዕልፍኝእስካገባው ድረስ አልለቀውም።

5. እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣በሚዳቋና በሜዳ ዋልያ አማጥናችኋለሁ።

6. ከከርቤና ከዕጣን፣ከነጋዴም ቅመማ ቅመም ሁሉ በተዘጋጀ ሽቱ፣መዐዛዋ የሚያውድ፣እንደ ጢስ ዐምድ ከምድረ በዳ የምትዋጣው ይህች ማን ናት?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 3