ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 3:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሌሊቱን ሙሉ በአልጋዬ ላይ ሆኜ፣ውዴን ተመኘሁ፤ተመኘሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።

2. ተነሥቼ ወደ ከተማዪቱ እወጣለሁ፤በዋና ዋና መንገዶችና በአደባባዮች እዘዋወራለሁ፤ውዴንም እፈልገዋለሁ፤ስለዚህም ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።

3. በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣የከተማዪቱ ጠባቂዎች አገኙኝ፤እኔም፣ “ውዴን አይታችኋል?”አልኋቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 3