ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 7:5-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ባልንጀራህን አትመን፤በጓደኛህም አትታመን፤በዕቅፍህ ለምትተኛዋ እንኳ፣ስለምትነግራት ቃል ተጠንቀቅ።

6. ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃል፤ሴት ልጅ በእናቷ ላይ፤ምራት በአማቷ ላይ ትነሣለች፤የሰው ጠላቶች የገዛ ቤተ ሰዎቹ ናቸውና።

7. እኔ ግን እግዚአብሔርን ተስፋ አደርጋለሁ፤አዳኜ የሆነውን አምላክ እጠብቃለሁ፤አምላኬ ይሰማኛል።

8. ጠላቴ ሆይ፤ በእኔ ላይ በደረሰው ደስ አይበልሽ!ብወድቅም እንኳ እነሣለሁ፤በጨለማ ብቀመጥ እንኳ፣ እግዚአብሔር ብርሃኔ ይሆናል።

9. እርሱን ስለ በደልሁ፣እስኪቆምልኝእስኪፈርድልኝም ድረስ፣ የእግዚአብሔርን ቊጣ እቀበላለሁ፤እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤እኔም ጽድቁን አያለሁ።

10. ጠላቴም ታያለች፤ኀፍረትንም ትከናነባለች፤“አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?”ያለችኝን፣ዐይኖቼ ውድቀቷን ያያሉ፤አሁንም እንኳ፣እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።

11. ቅጥሮቻችሁን የምትሠሩበት፣ድንበራችሁንም የምታሰፉበት ቀን ይመጣል።

12. በዚያ ቀን ሰዎች፣ከአሦር እስከ ግብፅ ከተሞች፣ከግብፅ እስከ ኤፍራጥስ፣ከባሕር ወደ ባሕር፣ከተራራ ወደ ተራራ ወደ እናንተ ይመጣሉ።

13. ከሥራቸው የተነሣ፣በነዋሪዎቿ ምክንያት ምድር ባድማ ትሆናለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 7