ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 7:15-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. “ከግብፅ እንደ ወጣህበት ዘመን ሁሉ፣ታምራቴን አሳያቸዋለሁ።”

16. አሕዛብ ያያሉ፣ ያፍራሉም፤ኀይላቸውን ሁሉ ያጣሉ፤አፋቸውን በእጃቸው ይይዛሉ፤ጆሮአቸውም ትደነቍራለች።

17. በደረታቸው እንደሚሳቡ ፍጥረታት፣እንደ እባብም ትቢያ ይልሳሉ፤ከዋሻቸው እየተንቀጠቀጡ ይወጣሉ፤በፍርሀትም ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤እናንተንም ይፈራሉ።

18. የርስቱን ትሩፍ፣ኀጢአት ይቅር የሚል፣ የሚምርእንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው?ለዘላለም አትቈጣም፤ነገር ግን ምሕረት በማድረግ ደስ ይልሃል።

19. ተመልሰህ ትራራልናለህ፤ኀጢአታችንን በእግርህ ትረግጣለህ፤በደላችንንም ሁሉ ወደ ጥልቁ ባሕር ትጥላለህ።

20. ከቀድሞ ዘመን ጀምሮለአባቶቻችን በመሐላ ቃል እንደ ገባህላቸው፣ለያዕቆብ ታማኝነትን፣ለአብርሃምም ምሕረትን ታደርጋለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 7