ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 7:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ብቻቸውን በዱር ውስጥ፣በለመለመ መስክ የሚኖሩትን፣የርስትህ መንጋ የሆኑትን፣ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤እንደ ቀድሞው ዘመን፣በባሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።

15. “ከግብፅ እንደ ወጣህበት ዘመን ሁሉ፣ታምራቴን አሳያቸዋለሁ።”

16. አሕዛብ ያያሉ፣ ያፍራሉም፤ኀይላቸውን ሁሉ ያጣሉ፤አፋቸውን በእጃቸው ይይዛሉ፤ጆሮአቸውም ትደነቍራለች።

17. በደረታቸው እንደሚሳቡ ፍጥረታት፣እንደ እባብም ትቢያ ይልሳሉ፤ከዋሻቸው እየተንቀጠቀጡ ይወጣሉ፤በፍርሀትም ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤እናንተንም ይፈራሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 7