ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 7:13-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ከሥራቸው የተነሣ፣በነዋሪዎቿ ምክንያት ምድር ባድማ ትሆናለች።

14. ብቻቸውን በዱር ውስጥ፣በለመለመ መስክ የሚኖሩትን፣የርስትህ መንጋ የሆኑትን፣ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤እንደ ቀድሞው ዘመን፣በባሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።

15. “ከግብፅ እንደ ወጣህበት ዘመን ሁሉ፣ታምራቴን አሳያቸዋለሁ።”

16. አሕዛብ ያያሉ፣ ያፍራሉም፤ኀይላቸውን ሁሉ ያጣሉ፤አፋቸውን በእጃቸው ይይዛሉ፤ጆሮአቸውም ትደነቍራለች።

17. በደረታቸው እንደሚሳቡ ፍጥረታት፣እንደ እባብም ትቢያ ይልሳሉ፤ከዋሻቸው እየተንቀጠቀጡ ይወጣሉ፤በፍርሀትም ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤እናንተንም ይፈራሉ።

18. የርስቱን ትሩፍ፣ኀጢአት ይቅር የሚል፣ የሚምርእንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው?ለዘላለም አትቈጣም፤ነገር ግን ምሕረት በማድረግ ደስ ይልሃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 7