ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 6:14-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ትበላለህ፤ ነገር ግን አትጠግብም፤ሆድህ እንዳለ ባዶውን ይቀራል፤ታከማቻለህ፤ ነገር ግን አይጠራቀምልህም፤የሰበሰብኸውን ለሰይፍ አደርገዋለሁና።

15. ትዘራለህ፤ ነገር ግን አታጭድም፤የወይራ ዘይት ትጨምቃለህ፤ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፤ወይንን ትቈርጣለህ፤ ነገር ግን የወይን ጠጅ አትጠጣም።

16. የዖምሪን ሥርዐት፣የአክዓብን ቤት ልምድ ሁሉ የሙጥኝ ብለሃል፤ትውፊታቸውንም ተከትለሃል።ስለዚህ አንተን ለውድመት፣ሕዝብህን ለመዘባበቻ አሳልፌ እሰጣለሁ፤አሕዛብም ይሣለቁብሃል።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 6