ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 5:8-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣በእግሩ እየጨፈላለቀ እንደሚሄድ፣የሰበረውን ማንም ሊነጥቀው እንደማይችል፣በበግ መንጋ መካከል እንዳለ፣እንደ ደቦል አንበሳ ሁሉ፣የያዕቆብም ትሩፍ፣ በአሕዛብ ዘንድ፣ በብዙም ሕዝብ መካከል እንደዚሁ ይሆናል።

9. እጅህ በጠላቶችህ ላይ በድል አድራጊነት ከፍ ከፍ ትላለች፤ጠላቶችህም ሁሉ ይጠፋሉ።

10. “በዚያን ጊዜ” ይላል እግዚአብሔር፤“ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ሠረገሎቻችሁን እደመስሳለሁ።

11. የምድራችሁን ከተሞች እደመስሳለሁ፤ምሽጎቻችሁንም ሁሉ አፈርሳለሁ።

12. ጥንቈላችሁን አጠፋለሁ፤ከእንግዲህም አታሟርቱም።

13. የተቀረጹ ምስሎቻችሁን፣የማምለኪያ ዐምዶቻችሁንም ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ከእንግዲህ ለእጃችሁ ሥራአትሰግዱም።

14. የአሼራ ምስልን ዐምድ ከመካከላችሁ እነቅላለሁ፤ከተሞቻችሁንም እደመስሳለሁ።

15. ያልታዘዙኝን አሕዛብ፣በቍጣና በመዓት እበቀላቸዋለሁ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 5