ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 5:5-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እርሱም ሰላማቸው ይሆናል።አሦራዊ ምድራችንን ሲወር፣ምሽጐቻችንንም ጥሶ ሲገባ፣ሰባት እረኞችን፣እንዲያውም ስምንት አለቆችን እናስነሣበታለን።

6. የአሦርን ምድር በሰይፍ፣የናምሩድን ምድር በተመዘዘ ሰይፍ ይገዛሉ፤አሦራዊው ምድራችንን ሲወር፣ዳር ድንበራችንን ሲደፍር፣እርሱ ነጻ ያወጣናል።

7. የያዕቆብ ትሩፍ፣በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣በሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ፣ሰውን እንደማይጠብቅ፣የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ሰው ይሆናል።

8. በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣በእግሩ እየጨፈላለቀ እንደሚሄድ፣የሰበረውን ማንም ሊነጥቀው እንደማይችል፣በበግ መንጋ መካከል እንዳለ፣እንደ ደቦል አንበሳ ሁሉ፣የያዕቆብም ትሩፍ፣ በአሕዛብ ዘንድ፣ በብዙም ሕዝብ መካከል እንደዚሁ ይሆናል።

9. እጅህ በጠላቶችህ ላይ በድል አድራጊነት ከፍ ከፍ ትላለች፤ጠላቶችህም ሁሉ ይጠፋሉ።

10. “በዚያን ጊዜ” ይላል እግዚአብሔር፤“ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ሠረገሎቻችሁን እደመስሳለሁ።

11. የምድራችሁን ከተሞች እደመስሳለሁ፤ምሽጎቻችሁንም ሁሉ አፈርሳለሁ።

12. ጥንቈላችሁን አጠፋለሁ፤ከእንግዲህም አታሟርቱም።

13. የተቀረጹ ምስሎቻችሁን፣የማምለኪያ ዐምዶቻችሁንም ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ከእንግዲህ ለእጃችሁ ሥራአትሰግዱም።

14. የአሼራ ምስልን ዐምድ ከመካከላችሁ እነቅላለሁ፤ከተሞቻችሁንም እደመስሳለሁ።

15. ያልታዘዙኝን አሕዛብ፣በቍጣና በመዓት እበቀላቸዋለሁ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 5