ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 5:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. የምድራችሁን ከተሞች እደመስሳለሁ፤ምሽጎቻችሁንም ሁሉ አፈርሳለሁ።

12. ጥንቈላችሁን አጠፋለሁ፤ከእንግዲህም አታሟርቱም።

13. የተቀረጹ ምስሎቻችሁን፣የማምለኪያ ዐምዶቻችሁንም ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ከእንግዲህ ለእጃችሁ ሥራአትሰግዱም።

14. የአሼራ ምስልን ዐምድ ከመካከላችሁ እነቅላለሁ፤ከተሞቻችሁንም እደመስሳለሁ።

15. ያልታዘዙኝን አሕዛብ፣በቍጣና በመዓት እበቀላቸዋለሁ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 5