ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 80:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣የእስራኤል እረኛ ሆይ፤ ስማን፤በኪሩቤል ላይ በዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፤በብርሃንህ ተገለጥ፤

2. በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት ደምቀህ ታይ።ኀይልህን አንቀሳቅስ፤መጥተህም አድነን።

3. አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤እንድንም ዘንድ፣ፊትህን አብራልን።

4. የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤በሕዝብህ ጸሎት ላይ ቍጣህ የሚነደው፣እስከ መቼ ድረስ ነው?

5. የእንባ እንጀራ አበላሃቸው፤ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው።

6. ለጎረቤቶቻችን የጠብ ምክንያት አደረግኸን፤ጠላቶቻችንም ተሣሣቁብን።

7. የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤እንድንም ዘንድ፣ፊትህን አብራልን።

8. ከግብፅ የወይን ግንድ አመጣህ፤አሕዛብን አባርረህ እርሷን ተከልሃት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 80