ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 74:2-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ጥንት ገንዘብህ ያደረግሃትን ጉባኤ፣የዋጀሃትን የርስትህን ነገድ፣መኖሪያህ ያደረግሃትን የጽዮን ተራራ አስብ።

3. እርምጃህን ለዘላለሙ ባድማ ወደ ሆነው አቅና፤ጠላት በመቅደስህ ውስጥ ያለውን ሁሉ አበላሽቶአል።

4. ጠላቶችህ በመገናኛ ስፍራህ መካከል ደነፉ፤አርማቸውንም ምልክት አድርገው በዚያ አቆሙ።

5. በጫካ መካከል ዛፎችን ለመቍረጥ፣መጥረቢያ የሚያነሣ ሰው መሰሉ።

6. በእደ ጥበብ ያጌጠውን ሥራ ሁሉ፣በመጥረቢያና በመዶሻ ሰባበሩት።

7. መቅደስህን አቃጥለው አወደሙት፤የስምህንም ማደሪያ አረከሱ።

8. በልባቸውም፣ “ፈጽሞ እንጨቍናቸዋለን” አሉ፤እግዚአብሔር በምድሪቱ ላይ የተመለከበትን ስፍራ ሁሉ አቃጠሉ።

9. የምናየው ምልክት የለም፤ከእንግዲህ የሚነሣ አንድም ነቢይ የለም፤ይህ እስከ መቼ እንደሚቀጥል የሚያውቅ በእኛ ዘንድ የለም።

10. አምላክ ሆይ፤ ጠላት የሚያሾፈው እስከ መቼ ነው?ባላንጣስ ለዘላለም በስምህ ያላግጣልን?

11. እጅህን ለምን ትሰበስባለህ?ቀኝ እጅህን ለምን በብብትህ ሥር ታቆያለህ?

12. አምላክ ሆይ፤ አንተ ከጥንት ጀምሮ ንጉሤ ነህ፤በምድር ላይ ማዳንን አደረግህ።

13. ባሕርን በኀይልህ የከፈልህ አንተ ነህ፤የባሕሩንም አውሬ ራሶች በውሃ ውስጥ ቀጠቀጥህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 74