ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 74:11-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እጅህን ለምን ትሰበስባለህ?ቀኝ እጅህን ለምን በብብትህ ሥር ታቆያለህ?

12. አምላክ ሆይ፤ አንተ ከጥንት ጀምሮ ንጉሤ ነህ፤በምድር ላይ ማዳንን አደረግህ።

13. ባሕርን በኀይልህ የከፈልህ አንተ ነህ፤የባሕሩንም አውሬ ራሶች በውሃ ውስጥ ቀጠቀጥህ።

14. የሌዋታንን ራሶች አደቀቅህ፤ለምድረ በዳ ፍጥረታትም ምግብ አድርገህ የሰጠሃቸው፣

15. ምንጮችንና ፈሳሾችን ያፈለቅህ አንተ ነህ፤ሳያቋርጡ የሚፈሱትንም ወንዞች አደረቅህ።

16. ቀኑ የአንተ ነው፤ ሌሊቱም የአንተ ነው፤ጨረቃንና ፀሓይን አንተ አጸናሃቸው።

17. የምድርን ዳርቻ ሁሉ የወሰንህ አንተ ነህ፤በጋውንም ክረምቱንም አንተ ሠራህ።

18. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላት እንዴት እንደሚያሾፍ፣ከንቱ ሕዝብም ስምህን እንዴት እንዳቃለለ አስብ።

19. የርግብህን ነፍስ አሳልፈህ ለዱር አራዊት አትስጥ፤የችግረኞች ሕዝብህን ሕይወት ለዘላለሙ አትርሳ።

20. ኪዳንህን አስብ፤የዐመፅ መናኸሪያ በምድሪቱ ጨለማ ስፍራዎች ሞልተዋልና።

21. የተጨቈኑት አፍረው አይመለሱ፤ድኾችና ችግረኞች ስምህን ያመስግኑ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 74