ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 74:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ ለዘላለም የጣልኸን ለምንድን ነው?በማሰማሪያህ ባሉ በጎችህስ ላይ ቍጣህ ለምን ነደደ?

2. ጥንት ገንዘብህ ያደረግሃትን ጉባኤ፣የዋጀሃትን የርስትህን ነገድ፣መኖሪያህ ያደረግሃትን የጽዮን ተራራ አስብ።

3. እርምጃህን ለዘላለሙ ባድማ ወደ ሆነው አቅና፤ጠላት በመቅደስህ ውስጥ ያለውን ሁሉ አበላሽቶአል።

4. ጠላቶችህ በመገናኛ ስፍራህ መካከል ደነፉ፤አርማቸውንም ምልክት አድርገው በዚያ አቆሙ።

5. በጫካ መካከል ዛፎችን ለመቍረጥ፣መጥረቢያ የሚያነሣ ሰው መሰሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 74