ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 55:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እኔም እንዲህ አልሁ፤ “ምነው የርግብ ክንፍ በኖረኝ!በርሬ በሄድሁና ባረፍሁ ነበር፤

7. እነሆ፤ ኰብልዬ በራቅሁ፣በምድረ በዳም በሰነበትሁ ነበር፤ ሴላ

8. ከዐውሎ ነፋስና ከውሽንፍር ሸሽቼ፣ወደ መጠለያዬ ፈጥኜ በደረስሁ ነበር።”

9. ጌታ ሆይ፤ ግፍንና ሁከትን በከተማዪቱ ውስጥ አይቼአለሁና፣ግራ አጋባቸው፤ ቋንቋቸውንም ደበላልቅ።

10. ቀንና ሌሊት ቅጥሯ ላይ ወጥተው ይዞሯታል፤ተንኰልና መከራ በውስጧ አለ።

11. ጥፋት በመካከሏ ይገኛል፤ግፍና አታላይነትም ከጎዳናዋ አይጠፋም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 55