ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 55:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. በማታ፣ በጥዋትና በቀትር፣እጮኻለሁ፤ እቃትታለሁም፤እርሱም ድምፄን ይሰማል።

18. በተቃውሞ የተነሡብኝ ብዙዎች ናቸውና፣ከተቃጣብኝ ጦርነት፣ነፍሴን በሰላም ይቤዣታል።

19. አካሄዳቸውን አልቀየሩምና፣እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና፣ከጥንት ጀምሮ በዙፋኑ ላይ ያለ አምላክ፣ ሴላሰምቶ ያዋርዳቸዋል።

20. ባልንጀራዬ የምለው ሰው እጁንበወዳጆቹ ላይ ሰነዘረ፤ቃል ኪዳኑንም አፈረሰ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 55