ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 55:15-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ሞት ሳይታሰብ ድንገት ይምጣባቸው፤በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ይውረዱ፤ክፋት በመካከላቸው አድራለችና።

16. እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እጣራለሁ፤ እግዚአብሔርም ያድነኛል።

17. በማታ፣ በጥዋትና በቀትር፣እጮኻለሁ፤ እቃትታለሁም፤እርሱም ድምፄን ይሰማል።

18. በተቃውሞ የተነሡብኝ ብዙዎች ናቸውና፣ከተቃጣብኝ ጦርነት፣ነፍሴን በሰላም ይቤዣታል።

19. አካሄዳቸውን አልቀየሩምና፣እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና፣ከጥንት ጀምሮ በዙፋኑ ላይ ያለ አምላክ፣ ሴላሰምቶ ያዋርዳቸዋል።

20. ባልንጀራዬ የምለው ሰው እጁንበወዳጆቹ ላይ ሰነዘረ፤ቃል ኪዳኑንም አፈረሰ።

21. አፉ ከቅቤ ይልቅ የለዘበ ነው፤በልቡ ግን ጦርነት አለ፤ቃሉ ከዘይት ይልቅ የለሰለሰ ነው፤ይሁን እንጂ የተመዘዘ ሰይፍ ነው።

22. የከበደህን ነገር በእግዚአብሔር ላይ ጣል፤እርሱ ደግፎ ይይዝሃል፤የጻድቁንም መናወጥ ከቶ አይፈቅድም።

23. አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጒድጓድታወርዳቸዋለህ፤ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም።እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 55