ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 55:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. በእግዚአብሔርም ቤት አብረን በሕዝብ መካከል ተመላለስን፤ደስ የሚል ፍቅር በአንድነት ነበረን።

15. ሞት ሳይታሰብ ድንገት ይምጣባቸው፤በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ይውረዱ፤ክፋት በመካከላቸው አድራለችና።

16. እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እጣራለሁ፤ እግዚአብሔርም ያድነኛል።

17. በማታ፣ በጥዋትና በቀትር፣እጮኻለሁ፤ እቃትታለሁም፤እርሱም ድምፄን ይሰማል።

18. በተቃውሞ የተነሡብኝ ብዙዎች ናቸውና፣ከተቃጣብኝ ጦርነት፣ነፍሴን በሰላም ይቤዣታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 55