ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 55:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ቀንና ሌሊት ቅጥሯ ላይ ወጥተው ይዞሯታል፤ተንኰልና መከራ በውስጧ አለ።

11. ጥፋት በመካከሏ ይገኛል፤ግፍና አታላይነትም ከጎዳናዋ አይጠፋም።

12. የሚዘልፈኝ ጠላት አይደለምና፤ቢሆንማ ኖሮ በታገሥሁት ነበር፤የሚጠላኝ፣ ራሱንም ቀና ቀና ያደረገብኝ ባላንጣ አይደለም፤ቢሆንማ ከእርሱ በተሸሸግሁ ነበር።

13. ነገር ግን አድራጊው አንተ ነህ፤ እኩያዬ፣ ባልንጀራዬና ወዳጄ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 55