ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 22:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ አጮኻለሁ፤አንተ ግን አልመለስህልኝም፤በሌሊት እንኳ አላረፍሁም።

3. አንተ ግን ቅዱሱ ነጋሢ፤የእስራኤልም ምስጋና ነህ።

4. አባቶቻችን በአንተ ታመኑ፤ተማመኑብህ፤ አንተም ታደግሃቸው።

5. ወደ አንተ ጮኹ፤ ዳኑም፤በአንተም ታመኑ፤ አላፈሩም።

6. እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤ሰው ያላገጠብኝ፣ ሕዝብም የናቀኝ ነኝ።

7. የሚያዩኝ ሁሉ ይሣለቁብኛል፤ራሳቸውንም እየነቀነቁ እንዲህ እያሉ ይዘልፉኛል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 22