ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 22:2-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ አጮኻለሁ፤አንተ ግን አልመለስህልኝም፤በሌሊት እንኳ አላረፍሁም።

3. አንተ ግን ቅዱሱ ነጋሢ፤የእስራኤልም ምስጋና ነህ።

4. አባቶቻችን በአንተ ታመኑ፤ተማመኑብህ፤ አንተም ታደግሃቸው።

5. ወደ አንተ ጮኹ፤ ዳኑም፤በአንተም ታመኑ፤ አላፈሩም።

6. እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤ሰው ያላገጠብኝ፣ ሕዝብም የናቀኝ ነኝ።

7. የሚያዩኝ ሁሉ ይሣለቁብኛል፤ራሳቸውንም እየነቀነቁ እንዲህ እያሉ ይዘልፉኛል፤

8. “በእግዚአብሔር ተማምኖአል፤እንግዲህ እርሱ ያድነው፤ደስ የተሰኘበትን፣እስቲ ይታደገው።”

9. አንተ ግን ከማሕፀን አወጣኸኝ፤በእናቴም ጡት ሳለሁ፣ መታመኛ ሆንኸኝ።

10. ከማሕፀን ስወጣም በአንተ ላይ ተጣልሁ፤ከእናቴ ሆድ ጀምሮም አንተ አምላኬ ነህ።

11. መከራ እየተቃረበ ነውና፣የሚረዳኝም የለምና፣ከእኔ አትራቅ።

12. ብዙ ኰርማዎች ከበቡኝ፤ኀይለኛ የባሳን በሬዎችም ዙሪያዬን ቆሙ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 22