ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 22:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?እኔን ከማዳን፣ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ?

2. አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ አጮኻለሁ፤አንተ ግን አልመለስህልኝም፤በሌሊት እንኳ አላረፍሁም።

3. አንተ ግን ቅዱሱ ነጋሢ፤የእስራኤልም ምስጋና ነህ።

4. አባቶቻችን በአንተ ታመኑ፤ተማመኑብህ፤ አንተም ታደግሃቸው።

5. ወደ አንተ ጮኹ፤ ዳኑም፤በአንተም ታመኑ፤ አላፈሩም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 22