ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 18:45-50 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

45. ባዕዳን በፍርሃት ተዋጡ፤ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ።

46. እግዚአብሔር ሕያው ነው! ዐምባዬ ይባረክ፤ያዳነኝ አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።

47. እርሱ በቀሌን የሚመልስልኝ፣ሕዝቦችንም የሚያስገዛልኝ አምላክ ነው፤

48. ከጠላቶቼም የሚታደገኝ እርሱ ነው።አንተ ከባላንጦቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ከጨካኞች አዳንኸኝ።

49. እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ስምህንም በመዝሙር እወድሳለሁ።

50. እርሱ ላነገሠው ታላላቅ ድሎችን ይሰጣል፤ጽኑ ፍቅሩንም ለቀባው፣ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይገልጣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 18