ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 18:34-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል፤ክንዴም የናስ ቀስት መገተር ይችላል።

35. የድል ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች፤ዝቅ ብለህም ከፍ አደረግኸኝ።

36. ከሥሬ ያለውን ስፍራ ለአረማመዴ አሰፋህልኝ፤እግሬም አልተንሸራተተም።

37. ጠላቶቼን አሳድጄ ያዝኋቸው፤እስኪጠፉም ወደ ኋላዬ አልተመለስሁም።

38. እንዳያንሰራሩ አድርጌ አደቀቅኋቸው፤ከእግሬም ሥር ወደቁ።

39. አንተ ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፤ባላንጦቼ እግሬ ላይ እንዲደፉ አደረግህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 18