ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 18:32-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣መንገዴንም የሚያቃና እግዚአብሔር ነው።

33. እርሱ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያደርጋል፤በከፍታዎችም ላይ ያቆመኛል።

34. እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል፤ክንዴም የናስ ቀስት መገተር ይችላል።

35. የድል ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች፤ዝቅ ብለህም ከፍ አደረግኸኝ።

36. ከሥሬ ያለውን ስፍራ ለአረማመዴ አሰፋህልኝ፤እግሬም አልተንሸራተተም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 18