ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 18:12-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ፣ደመናት፣ የበረዶ ድንጋይና መብረቅ ወጡ።

13. እግዚአብሔር ከሰማያት አንጐደጐደ፤ልዑልም ድምፁን አስተጋባ።

14. ፍላጻውን አስፈንጥሮ በተናቸው፤መብረቅ አዥጐድጒዶ አሳደዳቸው።

15. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከተግሣጽህ የተነሣ፣ከአፍንጫህም እስትንፋስ የተነሣ፣የባሕር ወለል ተገለጠ፤የዓለምም መሠረት ራቍቱን ቀረ።

16. ከላይ እጁን ወደ ታች ዘርግቶ ያዘኝ፤ከብዙ ጥልቅ ውሃም አወጣኝ፤

17. ከኀያላን ጠላቶቼ አዳነኝ፤ከእኔ ከሚበረቱ ባላንጣዎቼም ታደገኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 18