ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 17:7-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ከጠላቶቻቸው መተገኛ ያደረጉህን፣በቀኝ እጅህ የምትታደግ ሆይ፤ጽኑ ፍቅርህን ድንቅ አድርገህ ግለጥ።

8. እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤በክንፎችህም ጥላ ሰውረኝ፤

9. ከሚያስጨንቁኝ ከክፉዎች፣ከሚከብቡኝ አደገኛ ባላንጣዎቼ ጋርደኝ።

10. ደንዳና ልባቸውን ደፈኑት፤በአፋቸውም ትዕቢት ይናገራሉ።

11. አሳደው ደረሱብኝ፤ ከበቡኝም፤መሬት ላይ ሊዘርሩኝም አፈጠጡብኝ።

12. እነርሱ ለንጥቂያ እንደሚጓጓ አንበሳ፣በስውርም እንደሚያደባ ደቦል አንበሳ ናቸው።

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥተህ ግጠማቸውና ጣላቸው፤በሰይፍህም ከክፉዎች ታደገኝ።

14. እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲህ ካሉት ሰዎች በክንድህ አድነኝ፤ዕድል ፈንታቸው ይህችው ሕይወት ብቻ ከሆነች፣ ከዚህ ዓለም ሰዎች ታደገኝ።ከመዝገብህ ሆዳቸውን ሞላህ፤ልጆቻቸውም ተትረፍርፎላቸዋል፤ለልጆቻቸውም ሀብት ያከማቻሉ።

15. እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ስነቃም ክብርህን አይቼ እረካለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 17