ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 141:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ሹማምታቸው ከገደል አፋፍ ቍልቍል ይወረወራሉ፣ቃሌ የምታረካ ናትና፣ ይሰሟታል።

7. ደግሞም፣ “ሰው ምድርን እንደሚያርስና ዐፈሩን እንደሚፈረካክስ፣እንዲሁ ዐጥንታችን በሲኦል አፋፍ ላይ ተበታተነ” ይላሉ።

8. ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ፤መጠጊያዬም አንተ ነህ፤ እንግዲህ ነፍሴን አትተዋት።

9. ከዘረጉብኝ ወጥመድ፣ከክፉ አድራጊዎችም አሽክላ ጠብቀኝ።

10. እኔ ብቻ በደኅና ሳመልጥ፣ክፉዎቹ በገዛ ወጥመዳቸው ይውደቁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 141