ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 141:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ወደ አንተ ስጣራም ድምፄን ስማ።

2. ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን ትቈጠርልኝ፤እጄን ማንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን።

3. እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።

4. ከዐመፀኞች ጋር፣በክፉ ሥራ እንዳልተባበር፣ልቤን ወደ ክፉ አታዘንብል፤ከድግሳቸውም አልቋደስ።

5. ጻድቅ ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስ ዘይት ነው፤ራሴም ይህን እንቢ አይልም።ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው፤

6. ሹማምታቸው ከገደል አፋፍ ቍልቍል ይወረወራሉ፣ቃሌ የምታረካ ናትና፣ ይሰሟታል።

7. ደግሞም፣ “ሰው ምድርን እንደሚያርስና ዐፈሩን እንደሚፈረካክስ፣እንዲሁ ዐጥንታችን በሲኦል አፋፍ ላይ ተበታተነ” ይላሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 141