ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 136:9-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ጨረቃና ከዋክብት በሌሊት እንዲሠለጥኑ ያደረገ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

10. የግብፅን በኵር የመታ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

11. እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

12. በኀያል እጅና በተዘረጋች ክንድ ይህን ያደረገ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

13. የኤርትራን ባሕር ለሁለት የከፈለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

14. እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

15. ፈርዖንንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ያሰጠመ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

16. ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 136