ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 136:18-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ኀያላን ነገሥታትን የገደለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

19. የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን የገደለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

20. የባሳንን ንጉሥ ዐግን የገደለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

21. ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

22. ለባሪያው ለእስራኤል ርስት አድርጎ የሰጠ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

23. በውርደታችን ጊዜ ያሰበን፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

24. ከጠላቶቻችን እጅ ያዳነን፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

25. ለፍጡር ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

26. የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 136