ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 136:11-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

12. በኀያል እጅና በተዘረጋች ክንድ ይህን ያደረገ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

13. የኤርትራን ባሕር ለሁለት የከፈለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

14. እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

15. ፈርዖንንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ያሰጠመ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

16. ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

17. ታላላቅ ነገሥታትን የመታ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

18. ኀያላን ነገሥታትን የገደለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

19. የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን የገደለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

20. የባሳንን ንጉሥ ዐግን የገደለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

21. ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

22. ለባሪያው ለእስራኤል ርስት አድርጎ የሰጠ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 136