ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 109:22-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና፤ልቤም በውስጤ ቈስሎአልና።

23. እንደ ምሽት ጥላ ከእይታ ተሰውሬአለሁ፤እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ።

24. ከጾም የተነሣ ጒልበቴ ዛለ፤ሰውነቴም ከስቶ ዐመድ ለበሰ።

25. ለመሣለቂያ ሆንሁላቸው፤ሲያዩኝም ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።

26. እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ርዳኝ፤እንደ ምሕረትህም አድነኝ።

27. እግዚአብሔር ሆይ፤ እጅህ ይህን እንዳደረገች፣አንተም ይህን እንደ ፈጸምህ ይወቁ።

28. እነርሱ ይራገማሉ፤ አንተ ግን ትባርካለህ፤በሚነሡበት ጊዜ ይዋረዳሉ፤ባሪያህ ግን ሐሤት ያደርጋል።

29. የሚወነጅሉኝ ውርደትን ይከናነቡ፤ዕፍረትንም እንደ ሸማ ይልበሱ።

30. እግዚአብሔርን በአንደበቴ እጅግ አመሰግናለሁ፤በታላቅ ሕዝብም መካከል አወድሰዋለሁ።

31. በነፍሱ ላይ ከሚፈርዱት ያድነው ዘንድ፣እርሱ በችግረኛው ቀኝ በኩል ይቆማልና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 109