ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 109:11-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ያለውን ሁሉ ዕዳ ጠያቂ ይውረሰው፤የድካሙንም ዋጋ ባዕዳን ይቀሙት።

12. ማንም ሰው ምሕረት አያድርግለት፤ለድኻ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።

13. ዘሩ ተለይቶ ይጥፋ፤ስማቸውም በሚቀጥለው ትውልድ ይደምሰስ።

14. የአባቶቹ በደል በእግዚአብሔር ፊት ይታሰብ፤የእናቱም ኀጢአት አይደምሰስ።

15. መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፉ ዘንድ፣ኀጢአታቸው ሁል ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ይኑር፤

16. ችግረኛውንና ምስኪኑን፣ ልቡም የቈሰለውን፣እስከ ሞት አሳደደ እንጂ፣ምሕረት ያደርግ ዘንድ አላሰበምና።

17. መራገምን ወደደ፤ ወደ እርሱም መጣች፤በመባረክ ደስ አልተሰኘም፤በረከትም ከእርሱ ራቀች።

18. መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፤እርሷም እንደ ውሃ ወደ ውስጥ ሰውነቱ፤እንደ ዘይትም ወደ ዐጥንቱ ዘለቀች።

19. ገላውን እንደሚሸፍንበት ልብስ፣ዘወትር እንደሚታጠቀውም መቀነት ትሁነው።

20. እግዚአብሔር ለሚወነጅሉኝ ሰዎች፣በነፍሴም ላይ ክፉ ለሚናገሩ የሚከፍላቸው ይኸው ይሁን።

21. አንተ ግን ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ስለ ስምህ በበጎ ተመልከተኝ፤ምሕረትህም መልካም ናትና አድነኝ።

22. እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና፤ልቤም በውስጤ ቈስሎአልና።

23. እንደ ምሽት ጥላ ከእይታ ተሰውሬአለሁ፤እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 109