ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 102:23-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ብርታቴን መንገድ ላይ ቀጨው፤ዕድሜዬንም ባጭሩ አስቀረው።

24. እኔም እንዲህ አልሁ፤“አምላኬ ሆይ፤ በዘመኔ እኵሌታ አትውሰደኝ፤ዘመናትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራሉ።

25. አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፤ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።

26. እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፤እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፤እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ።

27. አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።

28. የአገልጋዮችህ ልጆች ተደላድለው ይኖራሉ፤ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 102