ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 102:16-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤በክብሩም ይገለጣል።

17. እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ልመናቸውንም አይንቅም።

18. ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣ይህ ለመጪው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤

19. “እግዚአብሔር በከፍታ ላይ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቶአልና፤ከሰማይም ሆኖ ምድርን አይቶአል፤

20. ይኸውም የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፣ሞት የተፈረደባቸውንም ያድን ዘንድ ነው።”

21. ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በጽዮን፣ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤

22. ይህም፣ ሕዝቦችና መንግሥታት፣ እግዚአብሔርን ለማምለክ በአንድነት ሲሰበሰቡ ይሆናል።

23. ብርታቴን መንገድ ላይ ቀጨው፤ዕድሜዬንም ባጭሩ አስቀረው።

24. እኔም እንዲህ አልሁ፤“አምላኬ ሆይ፤ በዘመኔ እኵሌታ አትውሰደኝ፤ዘመናትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራሉ።

25. አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፤ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።

26. እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፤እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፤እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ።

27. አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።

28. የአገልጋዮችህ ልጆች ተደላድለው ይኖራሉ፤ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 102