ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 102:14-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይሰኛሉ፤ለዐፈሯም ይሳሳሉ።

15. ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ስም፣የምድርም ነገሥታት ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ።

16. እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤በክብሩም ይገለጣል።

17. እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ልመናቸውንም አይንቅም።

18. ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣ይህ ለመጪው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤

19. “እግዚአብሔር በከፍታ ላይ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቶአልና፤ከሰማይም ሆኖ ምድርን አይቶአል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 102