ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 9:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ፍቅራቸው፣ ጥላቻቸው፣ቅናታቸውም ከጠፋ ቈይቶአል፤ከፀሓይ በታች በሚሆነው ነገር ሁሉ፣ፈጽሞ ዕጣ ፈንታ አይኖራቸውም።

7. ሂድ፤ ምግብህን በደስታ ብላ፤ ወይንህንም ልብህ ደስ ብሎት ጠጣ፤ ባደረግኸው ነገር እግዚአብሔር ደስ ብሎታልና።

8. ዘወትር ልብስህ ነጭ ይሁን፤ ራስህንም ዘወትር በዘይት ቅባ።

9. እግዚአብሔር ከፀሓይ በታች በሰጠህ በዚህ ትርጒም የለሽ የሕይወት ዘመን ሁሉ፣ ከንቱ በሆኑትም ቀኖችህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ፤ በሕይወትህና ከፀሓይ በታች በምትደክምበት ነገር ሁሉ ይህ ዕድል ፈንታህ ነውና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 9