ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 9:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለዚህ ይህን ሁሉ በልቤ አስቤ እንዲህ አልሁ፤ ጻድቃንና ጠቢባን የሚሠሩትም ሥራ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ነገር ግን ፍቅር ይሁን ወይም ጥላቻ የሚጠብቀውን ማንም አያውቅም።

2. ጻድቃንና ኀጥአን፣ ደጎችና ክፉዎች፣ ንጹሓንና ርኩሳን፣ መሥዋዕት የሚያቀርቡና የማያቀርቡ የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ አንድ ነው።ለደጉ ሰው እንደሆነው ሁሉ፣ለኀጢአተኛውም እንዲሁ ነው፤ለሚምሉት እንደሆነው ሁሉ፣መሐላን ለሚፈሩትም እንዲሁ ነው።

3. ከፀሓይ በታች በሁሉም ላይ የሚሆነው ክፋት ይህ ነው፤ የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ አንድ ነው። በዚህም ላይ የሰዎች ልብ በክፋት የተሞላ ነው፤ በሕይወት እያሉም በልባቸው ውስጥ እብደት አለ፤ በመጨረሻም ወደ ሙታን ይወርዳሉ።

4. በሕያዋን መካከል ያለ ማንኛውም ሰው ተስፋ አለው፤ በሕይወት ያለ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና!

5. ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ሙታን ግን ምንም አያውቁምና፤መታሰቢያቸው ይረሳል፤ምንም ዋጋ የላቸውም።

6. ፍቅራቸው፣ ጥላቻቸው፣ቅናታቸውም ከጠፋ ቈይቶአል፤ከፀሓይ በታች በሚሆነው ነገር ሁሉ፣ፈጽሞ ዕጣ ፈንታ አይኖራቸውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 9