ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 5:15-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ሰው ከእናቱ ማሕፀን ዕራቊቱን ይወለዳል፤እንደ መጣው እንዲሁ ይመለሳል።ከለፋበትም ነገር፣አንድም እንኳ በእጁ ይዞ ሊሄድ አይችልም።

16. ይህ ደግሞ እጅግ ክፉ ነገር ነው፤ሰው እንደ መጣ እንዲሁ ይሄዳል፤የሚደክመው ለነፋስ ስለ ሆነ፣ትርፉ ምንድ ነው?

17. በብዙ ጭንቀት፣ መከራና ብስጭት፣ዘመኑን ሁሉ በጨለማ ውስጥ ይበላል።

18. የሰው ዕጣው ይህ ስለ ሆነ፣ እግዚአብሔር በሰጠው በጥቂት ዘመኑ ከፀሓይ በታች በሚደክምበት ነገር ርካታን ያገኝ ዘንድ፣ መብላቱና መጠጣቱም መልካምና ተገቢ መሆኑን ተገነዘብሁ።

19. እግዚአብሔር ለሰው ባለጠግነትና ሀብት መስጠቱ፣ እንዲደሰትበትም ማስቻሉ፣ ዕጣውን እንዲቀበልና በሥራውም እንዲደሰት ማድረጉ፣ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።

20. እግዚአብሔር የልብ ደስታ ስለሚሰጠውም በሕይወቱ ዘመን ያሉትን ቀናት እምብዛም አያስባቸውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 5