ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 11:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እንጀራህን በውሃ ላይ ጣል፤ከብዙ ቀን በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህና።

2. ሀብትህን ሰባት ቦታ፣ እንዲያውም ስምንት ቦታ ከፍለህ አስቀምጥ፤በምድሪቱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት አታውቅምና።

3. ደመናት ውሃ ካዘሉ፣በምድር ላይ ዝናብን ያዘንባሉ፤ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ፣በወደቀበት ቦታ በዚያ ይጋደማል።

4. ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ደመናትንም የሚያይ አያጭድም።

5. የነፋስን መንገድ እንደማታውቅ፣ሕይወት ወይም መንፈስ በእናት ማሕፀን ውስጥ ወደሚገኘው አካል እንዴት እንደሚገባም እንደማታውቅ ሁሉ፣ሁሉን ሠሪ የሆነውን፣ የእግዚአብሔርን ሥራማስተዋል አትችልም።

6. ጠዋት ላይ ዘርህን ዝራ፤ማታም ላይ እጅህ ሥራ አይፍታ፤ይህ ወይም ያ፣ወይም ሁለቱ መልካም ይሁኑ፣የቱ እንደሚያፈራ አታውቅምና።

7. ብርሃን መልካም ነው፤ፀሓይንም ማየት ለዐይን ደስ ያሰኛል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 11