ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 1:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ወንዞች ሁሉ ወደ ባሕር ይፈሳሉ፤ባሕሩ ግን ፈጽሞ አይሞላም፤ወንዞች ወደ መጡበት ስፍራ፣ወደዚያ እንደ ገና ይመለሳሉ።

8. ሰው መናገር ከሚችለው በላይ፣ነገሮች ሁሉ አድካሚ ናቸው፤ዐይን ከማየት አይጠግብም፤ጆሮም በመስማት አይሞላም።

9. የነበረው ነገር እንደ ገና ይሆናል፤የተደረገውም ተመልሶ ይደረጋል፤ከፀሓይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም።

10. ማንም፣ “እነሆ፤ ይህ አዲስ ነገር ነው!”ሊል የሚችለው አንዳች ነገር አለን?ቀድሞውኑ በዚሁ የነበረ ነው፤ከእኛ በፊት የሆነ ነው።

11. የቀድሞ ነገሮች መታሰቢያ የላቸውም፤ወደ ፊት የሚመጡትም ቢሆኑ፣ከእነርሱ በኋላ በሚተኩት፣ አይታወሱም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 1